Pages

Friday, January 25, 2013

ምሥጢረ ጥምቀት

ምሥጢረ ጥምቀት

ጥምቀት ማለት ከውሃ ውስጥ መጥለቅ መነከር መጠመቅ ማለት ነው። ጥምቀት አጠመቀ ከሚለው ግስ የመጣ ሲሆን በገቢር መንከር መድፈቅ፣ አካልን ውሃ ውስጥ ማስገባት ማለት ነው ። ጥምቀት ሌሎችን ሚስጢራተ ቤተክርስቲያን ለመሳተፍ የቤተክርስቲያን አባል ለመሆን የመጀመሪያው መግቢያ በር ነው።
እግዚአብሔር ማንኛውንም ነገር ሲሰራ ትንቢት ያስነግራል ወይም ምሳሌ ያስቀድማል። በብሉይ ኪዳንም ለሀዲስ ኪዳን የተመሰሉ ምሳሌዎች አሉ። ከነዚህም ውስጥ ስለጥምቀት የተመሰሉ ምሳሌዎች
  • ኖህ ከጥፋት ወሃ ይድን ዘንድ መርከብ ሰራ ስለዚህ እርሱም ቤተሰቦቹም ወደ መርከቡ ገብተው የሰው ዘር ሁሉ ሲጠፋ ስምንት ሰዎች ብቻ ዳኑ። ይህም የጥምቀት ምሳሌ ነው። ኖህና ቤተሰቦቹ የምእመናን ፣ ባህሩ የጥምቀት ፣ መርከቡ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናቸው። ከመርከብ ወጭ የዳነ ሰው እንደሌለ በጥምቀት በር ያልገባ እና በቤተክርስቲያን ወስጥ ያልተገኘ አሁንም ድኅነት የለውም ሊኖረው አይችልም። ዘፍ 6፣1422 1ኛ ጴጥ 3፣20-21 ።
  • ግዝረተ አብርሃም የጥምቀት ምሳሌ ነው (ሮሜ 6፣18 ኤፌ 4፣18 ቆላ 2፣19-21 ቆላ 2፣9-12 ።
  • እስራኤላውያን ባህረ ኤርትራን መሻገራቸው ዘፍ 14፣14 -22 1ኛቆሮ 10፣1-2።
  • ኢዮብ በዮርዳኖስ ወንዝ መታጠቡ
  • ንዕማን የተባለው የሶሪያ ንጉሥ በዮርዳኖስ ወንዝ ታጥቦ ከለምጽ በሽታ መዳኑ 2ኛ ነገ 5፣1-16።
የጥምቀት አስፈላጊነት
  • ድህነት የሚገኘው በጥምቀት ነው በእምነት ብቻ አይደለም ማር፣10፣16 ሐዋ 2፣37 ሐዋ 8 ፣37።
  • በጥምቀት ዳግም ልደት ይገኛል(ዮሐ3፣5-8 ዮሐ 3.3)
  • ሥርየተ ኃጢአት ይገኛል ( ሐዋ 9፣15-16)
  • የክርስቶስ የሞቱና የትንሳኤው ተባባሪ መሆን ነው (ሮሚእ 6፣3-8)
  • አዲስ ህይወት ይገኛል (ሮሜ 6፣4)
  • የቤተክርስትያን አባል ለመሆን

የጥምቀት ስርዓት በ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ወንድ በተወለደ በአርባ ቀኑ ሴት በተወለደች በሰማንያ ቀኗ የጥምቀት ስርአት ይፈጸምላቸዋል የህጽኑ ጤንነት የሚያሰጋ ከሆነ ከዚህ ቀን በፊት ሊፈጸም ይችላል። በችግርና በሌላ ምክንያት ከተጠቀሰው ቀን ቢዘገይ ቤ/ክ የመጡትን ወደኃላ አትመልስም ታጠምቃለች።በ 40 እና በ80 ቀን የሆነበት ምክንያት አዳም በተፈጠረ በ40 ቀን ሔዋን በተፈጠረች በ80 ቀን ገነት እንዲገቡ ስለተፈቀደላቸው ነው (ኩፋ 4፣9)። እንዲሁም በኦሪት ይደረግ የነበረው ሥርዓት ለሃዲስ ምሳሌ በመሆኑ(ዘሌ12፣12 1-8. ሉቃ 2፣22)። ልጆችም እንደየጾታቸው በ 40 እና በ 80 ቀን የጸጋ ልጅነት ያገኛሉና ነው።(ዘሌ 12፣1-8)።
ወላጆች ተጠማቂውን ህጻን ይዘው ወደ ቢተክርስቲያን ይመጣሉ። ቄሱ ውሃውን በብረት(በርሜል) አድርጎ ስርአተ ጸሎቱን ይጀምራል፣ መጸሀፈ ክርስትና ይደግማል። በጸሎቱ መግቢያ ላይ የክርስትና እናት ወይም አባት ለመሆን የመጡ የህጻኑን አውራ ጣት ይዘው ተጠማቂውን ሊለው የሚገባውን ሶስት ጊዚ “እክህደከ ሰይጣን” እያሉ ያወግዛሉ ትርጉሙም ሰይጣንን ክጄዋለሁ ማለት ነው። ስርዓተ ጸሎቱ ተገባዶ ዲያቆኑ “ጸልዩ በእንተ ዛቲ ..” የሚለውን ጸሎት በዜማ ካዜመ በኋላ ጸሎተ ሃይማኖት ይደገማል። የሃይማኖት ጸሎትን ተጠማቂው፣ ተጠማቂው ህፃን ከሆነ የክርስትና አባት ወይም እናት የህጻኑን አውራ ጣት በመያዝ ሰለ ህጻኑ ፈንታ ይደግማሉ።
ተጠማቂው በቅዱሳን ስም ለቤተክርስትያን ከተሰጠ በእለቱ የሚያገለግለው ዲያቆን ጸሎተ ሃይማኖትን እየደገመ የህጻኑን አውራ ጣት ይይዛል።ይህ ሲፈጸም ይተጠማቂው ልብስ ይወልቃል በምዕራብ ፣ በሰሜን፣ በደቡብ፣ በምስራቅ እሰግድ ለአብ እሰግድ ለወልድ እሰግድ ለመንፈስ ቅዱስ እያለ ዲያቆኑ ተጠማቂውን በአራት አቅጣጫ እያሰገደ ያዞራል። በዚህ የስግደት ኡደት ጊዜ ካህኑም የተጠማቂውን ግንባር በመስቀል እያሻሸ “ስምከ ይኩን እገሌ” እያለ ስም በመሰየም ይባርከዋል።
ይህም ሲፈጸም ውሃውን ብሩክ ብሎ ባርኮ “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ውልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” ካለ በኋላ “አጠምቀከ በአብ አጠምቀከ በወልድ አጠምከከ በመንፈስ ቅዱስ እያለ ሶስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እያረገ ካህኑ ያጠምቃል። የክርስትና ስም አወጣጥም በ/ኢ/ኦ/ቤ/ክ ካህን የሚሰየመውን የእለት በአልን ምክንያት በማድረግ ነው። ለምሳሌ የጌታችን ፣የመቤታችን፣ እለት ከሆነ ገብረ መድኅን ኃ/ማርያም…የቅዱሳን መላእክት የፃድቃን ሰማእታት ከሆነ ወ/ሚካኤል ኃ/ጊዮርጊስ ወ.ዘ.ተ በሚል ስያሜ ይሰጠዋል።
ስያሜው ጥምቀት ሲያበቃ ካህኑ (ዲያቆኑ) ለክርስትና እናቱ(አባቱ) ያስረክባሉ። ከልጅህ (ከልጅሽ) የማትለየውና በክርስትያናዊ ምግባርና በሐይማኖት የምታሳድገው የቃል ኪዳን ልጅህ (ልጅሽ) ነው እያለ ካህኑ ይመክረዋል። እርሱም እሺ እያለ ይቀበላል በዚህ ጊዜ 36 ቦታዎች ሜሮን ይቀባል ይህብረት ቀለማት ያለው ፈትል ተገምዶ በአንገቱ ላይ ይታሰራል ይህ በግእዝ ማዕተብ በአማርኛ ቡራኬ(ስጦታ) ይባላል። ቀለሙ ሶስት ዓይነት ነው። ነጭ ቀይ፣ ቢጫ፣ (ነጭ የአብ ቀይ የወልድ ቢጫ የመንፈስ ቅዱስ ሶስት የመሆኑ ምስጢር ስላሴ አንድ ሆኖ መገመዱ የአንድ አምላክ መሳሌ ነው። ህፃኑ ልብሱን ከመልበሱ በፊት ቄሱ ህፃኑን በሁለት እጃቸው ከፍ አርገው ይይዙታል “ንሳ መንፈስ ቅዱስ” እየተባለ እፍ ይባልበታል። ከዚህ በኋላ ተጠማቂው ሜሮን ተቀብቶ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ይቆርባል የጥምቀቱ ስርዐት የሚፈጸውመው ተጠማቂው ሲቆርብ ብቻ ነው። አለበለዚያ ጥምቀቱ ሙሉ አይሆንም ምክንያቱም የጥምቀቱ ማህተብ ስጋወ ደሙ ነው።
ጥምቀት
ጥር 9 ቀን 2005 ዓ.ም
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ

በሰው ልጅ ዘላለማዊ ድኅነት ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው ሥርዓተ ጥምቀት ከሌሎቹ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በቀዳሚነት የሚፈጸምና የማይደገም ሥርዓት ነው፡፡ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ “አንዲት ጥመቀት” በማለት የሥርዓተ ጥምቀትን አለመደገምና አለመሠለስ ገልጦ ተናግሯል /ኤፌ.4፥5/፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ተመዝግቦ እንደሚገኘውና፥ የታናሽ እስያ ክፍል በሆነችው ቁስጥንጥንያ በ381 ዓ.ም. የተሰበሰቡ 150 የሃይማኖት አባቶቻችን “ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኀጢአት፣ ለኀጢአት ማስተሥረያ /ኀጢአትን በምታስተሠርይ/ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን” በማለት የጥምቀትን አንድ መሆንና ኀጢአትን በደልን የምታርቅ፣ የምታስወግድ ስለመሆኗ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ተመርተው ተናግረዋል፡፡ ሃይማኖታቸውንም ገልጠዋል፡፡

ጥምቀት የሚለውን ቃል አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ሲተረጉሙ “ጥምቀት” በቁሙ፡- “ማጥመቅ፣ መጠመቅ፣ አጠማመቅ፣ ጠመቃ፣ የማጥመቅና የመጠመቅ ሥራ፣ ኅፅበት፣ በጥሩ ውኃ የሚፈጸም” በማለት ተርጉመውታል፡፡ ምሥጢረ ጥምቀትን የመሠረተው ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ጌታችን ሥርዓተ ጥምቀትን የመሠረተው በሦስት ዓይነት መንገዶች እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡

ሦስቱ መንገዶች የሚባሉትም ትምህርት፣ ትዕዛዝና ተግባር ናቸው፡፡ ይኸውም ሊታወቅ በዮሐንስ ወንጌል ምዕ.3 ቁጥር 5 ላይ “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው፡፡ ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል ስላልሁህ አትደነቅ፡፡” በማለት የአይሁድ አለቃ ለነበረው ለኒቆዲሞስ ጌታችን ያስተማረውን ትምህርት ልብ ላለው ጥምቀት በጌታችን ትምህርት መመሥረቷን ይረዳል፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትዕዛዝም ጭምር ጥምቀትን መሥርቷል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ የጌታችንን ትዕዛዝ እንዲህ ያስነብበናል፡- “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፡፡” /ማቴ.28፥19/ መምህረ ትሕትና የሆነው መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተግባር መምህር ነውና ተጠመቁ ብሎ ካስተማረውና ካዘዘው በተጨማሪ ሥርዓተ ጥምቀትን በተግባር ጭምር መሥርቷል፡፡ በማቴዎስ ምዕራፍ 3 በማርቆስ ምዕራፍ 1 እና በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 3 ላይ በስፋት እንደተመዘገበው ጌታችንና አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ባሕረ ዮርደኖስ ሄዶ ከባሪያው ከዮሐንስ እጅ ሥርዓተ ጥምቀትን ፈጽሟል፡፡ በዚህም ትሕትናንና የትሕትናን አሠራር ፈጣሪያችን አሳይቷል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በበዓላት አከባበር ሥርዓት መሠረት በየዓመቱ ጥር 10 ቀን /የከተራ ዕለት/ ታቦታተ ሕጉ ከመንበረ ክብራቸው በመነሣት ወደ ጥምቀተ ባሕሩ ይጓዛሉ፡፡ ይህም ጌታችን በኪደተ እግሩ እየተመላለሰ ምድርን እንደቀደሳት በማሰብና እርሱኑ አርዓያ በማድረግ ሀገሩን መንደሩን ለመቀደስና ለመባረክ የሚፈጸም ዑደት ነው፡፡

ሥርዓተ ጥመቀት በአጋጣሚ ወይም በድንገት የተጀመረ /የተመሠረተ/ አይደለም፡፡ በዘመነ ብሉይ በርካታ ምሳሌዎች የተመሰሉለት፣ በርካታ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት ነው እንጂ፡፡ በነቢዩ ሕዝቅኤል እግዚአብሔር አምላካችን አድሮ ሲናገር “ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ፣ እናንተም ትጠራላችሁ ከርኲሰታችሁም ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አጠራችኋለሁ፡፡” ብሏል፡፡ /ሕዝ.36፥25/ ከኀጢአት የሚያነጻ ከርኲሰት የሚቀድስ ለመንግሥተ ሰማያት የሚያዘጋጅ የሚያበቃ ጥሩ ውኃ ተብሎ የተገለጸ ጥምቀት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡

ሥርዓተ ጥምቀትን የመሠረተው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመሆኑ በአጭሩ ከገለጽን፤ ጌታችን የተጠመቀው ለምንድር ነው? የሚል ጥያቄ ቢነሣ፡-

ጌታችን እርሱ ባወቀ ጥምቀትን የፈጸመበት ዋነኛ ምክንያቶች እንደ ሊቃውንት አባቶቻችን አስተምህሮ በሦስት መንገዶች ይታያል፡፡ እነዚህም

1ኛ ምሥጢረ ሥላሴን /ሦስትነቱን ያስረዳን ዘንድ ነው/ ማቴ.3፥13-17 በዘመነ ብሉይ በነበሩ ሰዎች በረቂቅና በምሳሌ ይታወቅ የነበረውን የልዩ ሦስትነቱንና አንድነቱን ምሥጢር በተረዳ በታወቀና በጎላ ሁኔታ እንረዳ ዘንድ ጌታችን ተጠምቋል፡፡ በቅዱስ ወንጌላችን በግልጽ እንደሚታየው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የስም፣ የአካል፣ የአካለ ግብር ሦስትነት እንዳላቸው በጊዜ ጥምቀቱ ለክርስቶስ እንረዳለን፡፡ ይኸውም እግዚአብሔር አብ በሰማይ ሆኖ፡- “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” በማለት እኔ ባይ አካል እንዳለው ገልጿል፡፡ እግዚአብሔር ወልድ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው ሰውነት በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ በዮሐንስ እጅ በመጠመቅ እርሱም እንደ ባሕርይ አባቱ የራሱ እኔ ባይ አካል እንዳለው ገልጦ አሳይቶናል፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ሆኖ ከሰማይ በመውረድ ታይቷል፤ በዚህም መንፈስ ቅዱስ እንደ አብና ወልድ እኔ ባይ አካል እንዳለው ተረድተናል፡፡ ስለሆነም ጌታችን ጥምቀትን የፈጸመው የሦስትነቱን ምሥጢር ይገልጽልን ዘንድ ነው፡፡

2ኛ ለትምህርት ለትሕትና ለአርዓያነት
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥርዓተ ጥምቀትን የፈጸመው እንደእኛ የሰው ልጆች የልጅነትን ጸጋ ለማግኘት አይደለም፡፡ እርሱ አብን በመልክ የሚመስለው በባሕርይ የሚተካከለው፤ ተቀዳሚም ተከታይም የሌለው የአብ የባሕርይ ልጁ ነውና፡፡ /ዮሐ.1፥18፣ ዮሐ.3፥16/ እንዲሁም እንደ ንዑስ ክርስቲያን ሥረየት ኃጢአትንም ለማግኘት አይደለም፡፡ ነውርም ኀጢአትም በደልም ምንም ምን ክፋት የሌለበት ንጹሐ ባሕርይ ነውና ነቢዩ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም እንዳለ /ኢሳ.53፥9፤ ማር.2፥10፣ ሉቃ.7፥49/ ነገር ግን በርዕሳችን እንደተገለጠው ጌታችን ሥርዓተ ጥምቀትን የፈጸመው ለትምህርት፣ ለትሐትናና ለአርአያነት ነው፡፡ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወትን የሚሰጥ እርሱ እንደ ደካማ ሰው ወደ ባሕረ ዮርዳኖስ ሄዶ ከዮሐንስ ዘንድ ሲጠመቅ ትሕትናን አስተምሮናል፡፡ ዮሐንስን መጥተህ አጥምቀኝ ሳይል ፤ ከዮሐንስ ዘንድ ሄዶ ተጠመቀ፡፡ የቱንም ያህል ክብር ሥልጦን…. ቢኖረን እኛም ከካህናት ዘንድ መሄድ እንዳለብን ሲያስተምረን ነው፤ /ዮሐ.131-17 እና 1ኛ ጴጥ.2፥26/

3ኛ. ጥምቀታችንን ይባርክልን ዘንድ
እንፈጽመው ዘንድ የሚገባንንና የሚያስፈልገንን ሥርዓት ሁሉ የሠራልን ፈጣሪያችን ነው፡፡ በገዳመ ቆሮንቶስ አርባ ቀን አርባ ሌሊት በመጾም ጾማችንን እንደባረከልን /ማቴ.4፥1-10/ በጥምቀቱ ጥምቀታችንን ይባርክልን ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመነ ሉቃስ በወርኀ ጥር በ11ኛው ቀን ማክሰኞ ሌሊት 10 ሰዓት ተጠምቋል፡፡

እኛ የሰው ልጆች ሥርዓተ ጥምቀት እንዲፈጸምልን የሚያስፈልገው፡-
የልጅነት ጸጋን እናገኝ ዘንድ ነው፡፡ ዮሐ.1፥5
አስቀድመን ከሥጋ እናት አባታችን በዘር በሩካቤ እንደተወለድንና የሥጋ ልጅነትን እንዳገኘን ሁሉ በማየ ገቦ ስንጠመቅ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ እንወለዳለን፡፡ ይህንን አስመልክቶ ጌታችን “ከሥጋ የሚወለድ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስ የሚወለድ መንፈስ ነው” ብሎ ከማስተማሩ በፊት “ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም” ያለው፡፡ /ዮሐ.3፥3 እና 6/ በምሥጢረ ጥምቀት ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና ስለመገኘቱ አስተምሯል፡፡ ሐዋርያውም በጥምቀት ስላገኘነው የልጅነት ጸጋ አስመልክቶ ሲናገር “አባ አባት ብለን የምንጮኸበትን /የምንጣራበትን/ የልጅነትን መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈስ ጋር ይመሰክራል፡፡” ብሏል፡፡ /ሮሜ.8፥15-16/ ጌታችንንም ለተቀበሉት ሁሉ በስሙም ላመኑበት በጠቅላላው የእግዚአብሔር ልጆች ይሁኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጥቷቸዋል፡፡ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አለመወለዳቸው ተገልጿል፡፡ /ዮሐ.1፥11-13/

እንግዲህ እኛ ክርስቲያኖች ሁለት ልደታት እንዳሉን እናስብ፡፡ ይኸውም መጀመሪያው ከሥጋ እናትና አባታችን የተወለድነው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ከእግዚአብሔር የምንወለደው ነው፡፡ ከተወለድን በኋላ እድገታችን በሁለቱም ወገን መሆን ያስፈልጋዋል፡፡ ሰው ሥጋዊም መንፈሳዊም ነውና፡፡

ሥርየተ ኀጢአትን ለማግኘት
በአምልኮ ባዕድና በልዩ ልዩ ሁኔታዎች ከጥምቀት በአፍአ ሆነው የቆዩ ሰዎች ከነበረባቸው ኀጢአት ይነፁ ዘንድ ሥርዓተ ጥምቀት ተሠርታለች፡፡ ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ በተነሣ በ50ኛው ቀን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ሀብቱ በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ ማደሩን የሰሙ አይሁድ፤ ከቅዱሳን ሐዋርየት ዘንድ ቀርበው የሚናገሩትን ቃለ እግዚአብሔር መስማት ጀመሩ፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የባሕርይ አምላክነቱን፣ በኃይለ ሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መነሣቱንና ወደ ሰማይ ማረጉን ነገሯቸው፡፡ አይሁድም ይህንን በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተነካ ጴጥሮስንና ሌሎችንም ሐዋርያት “ወንድሞች ሆይ ምን እናድርግ?” አሏቸው፡፡ ጴጥሮስም “ንስሐ ግቡ ኀጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ፡፡….” አላቸው /ሐዋ.2፥37-38/ ይህ የሐዋርያው ቃል የሚያስረዳን የጥምቀትን መድኀኒትነት ነው፡፡ አስቀድመን እንደገለጥነው አባቶቻችን በሃይማኖት መግለጫቸው “ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኀጢአት፥ ኀጢአትን በምታስተሠርይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን” ማለታቸው ጥምቀት ከደዌ ነፍስ የምታድን መሆኗን መመስከራቸው ነው፡፡ /ጸሎተ ሃይማኖት/

ዘላለማዊ ድኅነት
የሰው ልጅ ድኅነት ቅጽበታዊ አለመሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ይሁንና የድኅነት በር ከፋችና ሌሎችን ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ለመፈጸም የሚያበቃን ምሥጢር ምሥጢረ ጥምቀት ነው፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ደቀ መዛሙርቱ በሰጣቸው ሐዋርያዊ መመሪያ ውስጥ “ሑሩ ውስተ ኩሉ ዓለም ወስብኩ ወንጌለ ለኲሉ ፍጥረት፡፡ ዘአምነ ወዘተጠምቀ ይድኅን ወዘሰ ኢአምነ ይደየን፡፡ ወደ ዓለም ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ፡፡ ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል፡፡” በማለት ተናግሯል፡፡ /ማር.16፥15-16/

እንግዲህ በጥምቀት ያገኘነውን ጸጋና ክብር ሁላችን ልናስብ ያስፈልገናል፡፡ ይህንንም ክብራችንን መጠበቅ ያሻናል፡፡
ፈጣሪያችን በዓሉን የበረክት የረድኤት ያድርግልን፡፡

Sunday, January 6, 2013

“ቃልም ሥጋ ሆነ” [ ዮሐ 1-1 ]



እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን!
የጌታችንን ልደት ከብሥራት አንሥቶ በሰፊው የተረከልን ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ነው፡- “በዚያም ወራት ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ወጣችበማለት የልደቱን ዘገባ ይጀምራል፡፡ በወቅቱ ዓለምን ሁሉ የምትገዛው ሮም ነበረች፡፡ ንጉሠ ነገሥቱም ቄሣር በሚል መዐርግ ይጠራ ነበር፡፡ መንበሩም ያለው በሮም ሲሆን ዓለሙንም የሚያስተዳድረው በአጥቢያ ነገሥታት በኩል ነው፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ ዓለሙን የሚገዛው ከመንበሩ ሳይንቀሳቀስ ነው፡፡ በመልእክተኞቹ አማካይነት ዓለሙን ይገዛል፡፡ ጌታችን የተወለደው ከዘመን መርጦ በሮም አገዛዝ ዘመን ነው፡፡ የሮም አገዛዝ ለእግዚአብሔር መንግሥት ገላጭነት አለው፡፡ ይኸውም፡- እግዚአብሔር አብ ከሥፍራው ሳይናወጥ ይኖራል፤ ቃሉን ወይም ልጁን እንዲሁም መንፈስ ቅዱስን እየላከ ዓለምን ይገዛል፡፡ ወደዚህ ዓለም በሥጋ የመጣው እግዚአብሔር ወልድ ነው፡፡ እርሱ ካረገ በኋላም መንፈስ ቅዱስ መጥቷል። ክርስቶስ በትምህርቱ፣ በቤዛነቱ ዓለሙን ገዛ፡፡ መንፈስ ቅዱስም በጸጋው በተአምራቱ እንዲሁም በክርስቶስ ቃሎች ዓለምን ይገዛል፡፡ እንዲህ ሲሆን ግን የሥላሴ መንግሥት አንዲትና እኩል ናት፡፡

ድንግል
በድንግልና ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች [ኢሳ. 7.04]

በጥሊሞስ
ፈላደልፈስ &2 ሊቃውንትን በአሌክሳንድርያ አካባቢ በምትገኘው በፋሮስ ደሴት ላይ 72 ቀናት ውስጥ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን ከዕብራዊያን ወደ ጽርእ /ግሪክ/ እንዲተረጎሙ አደረገ። &2 ሊቃውን ሁለቱ መንገድ ላይ ሲሞቱ ሌሎቹ ሊቃውንት ብሉይ ኪዳንን ለመተርጉም እየገሰገሱ ንጉሥ  በጥሊሞስ ጋር ደረሱ!

ከደረሱት  & ሊቃውንት አንዱ አረጋዊ ስምኦን ነው። እነሆ ሰባው ሊቃውንት በሙሉ የየራሳቸውን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በእጆቻቸው ይዘዋል፤ አሁን ሊተረጉሙ ብዕራቸውን ሁሉም ያዙ!

ለአረጋዊ
ስምኦን የደረሰው የብሉይ ኪዳን ወንጌል እየተባለ የሚታወቀውትንቢተ ኢሳይያስነበር። ሊቁ አረጋዊ ስምኦንም እነሆ ትንቢተ ኢሳያስን ሊተረጉም ፩ዱ ብሎ ጀመረ። እስከ ፯ኛው ምዕራፍ በደህና ደረሰ፤ ምዕራፍ ላይ ሲደርስ ግን ሊቁ ግራ ተጋባ! እንዴት ሊሆን ይችላል እያለ ተገረመ! ምን ይሆን ያነበበው?


ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ወይሰመይ ስሙ አማኑኤልይህችን ቃል አነበበና አሁንም ሊቁ ተደመመ!!! እንዲህ ማለት ነበርና፦

ድንግል
በድንግልና ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች [ኢሳ. 7.04]

ድንግል
በድንግልና ትፀንሳለች! ከዚህ በፊት ሆኖ አያውቅም፤ በግዜውም አልተደረገም ወደፊትም አይደገምም አለና ሊቁ አሁንም ተደመመ! አሁን ድንግል በድንግልና ትፀንሳለች ብዬ ብተረጉመው አይደለም በጥሊሞስ የአሕዛብ ንጉሥ ቀርቶ የእስራኤል ንጉሥ ቢሆንስ ያምነኛልን? ብሎ ሊቁ አሰበ። እናም ድንግል ትፀንሳለች የሚለውን ሰርዞ ሴት ልጅ ትፀንሳለች ብሎ ፃፈው። ሊቁ ስምኦን እስከ ፯ኛው ምዕራፍ ስለፃፈ ደከመው መሰል ሸለብ አደረገው።

ትንሽ
እንዳረፈም ነቃ፤ ካቆመበት ሊቀጥል ቢል እነሆ የሰረዘው ተመልሶድንግል በድንግልና ትፀንሳለችየሚለውን አነበበ። በጣም ደክሞኛል ማለት ነው? የሰረዝኩት መስሎኝ ነበር አለና አሁንም ደግሞ ሰረዘውና አሸለበ። እንዲህ እያለድንግል በድንግልና ትፀንሳለችየሚለውን   ግዜ ቢሰርዘው   ግዜድንግል በድንግልና ትፀንሳለችየሚል ተጽፎ አነበበ።

በመጨረሻም
ሊቁ አረጋዊ ስምኦን የተጠራጠረውን ይህንድንግል በድንግልና ትፀንሳለችየሚለውን ቃል በዓይኑ ሳያይ እንደማይሞት መንፈስ ቅዱስ ገለፀለት። ስለዚህም ሉቃስ በወንጌሉ እንዲህ አለ፦ የጌታን መወለድ በዓይኑ ሳያይ እንደማይሞት መንፈስ ቅዱስ ያደረበትና የገለጠለት ሰው ነበር [ሉቃስ 2.!6]

አረጋዊው
ስምኦን እጅግ የተደነቀበትን ቃል 5)  ዓመታት ያህል በተስፋ ጠበቀ፤ እነሆ በዓይኑ የሚያይበት ግዜም ደረሰ፤ ይህም ጌታችን ከአንዲት 05 አመት ታናሽ ገሊላዊት ብላቴና በህቱም ድንግልና በቤተልሔም በኤፍራታ መወለዱ ነው!!!

ነቢዩ ኢሳያስ ስለ ፅዮን /ስለእመቤታችን/ ዝም አልልም እያለ በቤተልሔም ኤፍራታ ተገኘና የመላዕክቱን የእረኞቹን ዝማሬ ሰማናናሁ ድንግል ትፀንስእነሆ ድንግል በድንግልና ትፀንሳለች አለና የጌታን ልደት በዓይኑ ሊያይ ናፈቀና ትንቢቱ ከመፈፀሙ 7) ዓመታት በፊት አስቀድሞ  ተነበየ፤ የዘመኑ ሰዎች አልታደሉምና እንዴት ድንግል በድንግልና ትፀንሳለች አሉና መጋዝ አመጡና ኢሳያስን ያዙና እነሆ ሥጋውን ለሁለት በመጋዝ ቆራረጡት!
ነቢዩ ኢሳያስ የተነበየውን ትንቢት በዓይኑ አላየም። የኢሳያስን ትንቢት የተረጉመው አረጋዊ ስምኦን ግን በዓይኑ አየ፤ አንዳንድ ጊዜ እኛ ከምንናገረው ይልቅ ሰምተው የሚተረጉሙት የእግዚአብሔርን ቸርነት በዓይናቸው ያያሉ!
አረጋዊ ስምኦንድንግል በድንግልና ትፀንሳለችየሚለውን ትንቢት ተረጎመ በዓይኑም አየ አመነም! እንዲህም አለ ዓይኖቼ ማዳኑን አይተዋልና ይገባዋል ክብርና ምስጋናሉቃስ [2."]
የክርስቶስን ልደት ስናነሣ ፈረንጆቹ ስለ ገና አባትና ስለ ገና ዛፍ ስለ በረዶ ያስባሉ። በአገራችንም ስለ ገና ጨዋታ ይታሰባል፡፡ በአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናትም ገና የሕፃናት ነው ተብሎ ለሕፃናት ከረሜላ በማደል ይጠናቀቃል፡፡ የክርስቶስ ልደት ግን የመላው የሰው ዘር እንደገና የተወለደበት እንጂ ተራ የሕፃን በዓል አይደለም፡፡ የልደትን በዓል ማክበር ብቻውን ክርስቲያን አያሰኝም፡፡ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሆኑት የፍልስጤም አስተዳዳሪዎች የቀድሞ ያሲን አራፋት አሁን ደግሞ ማሕሙድ አባስ በቤተ ልሔም ተገኝተው ያከብሩታል፡፡ የእኛ አከባበር ከዚህ የላቀ ካልሆነ ድካም ብቻ ነው፡፡ የተወለደውን ሕጻን በቁሳቁስ ሳይሆን በሕይወታችን ልናከብረው፤ ደስታችንም በመብልና በመጠጥ ሳይሆን በፍቅሩ ሊሆን ይገባዋል፡፡
ብዙዎች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሰን እያሉ ይዘፍናሉ፣ ይጨፍራሉ፣ ይሰክራሉ፡፡ ክርስቶስ ግን የተወለደው ዘፈን፣ ኃጢአትና ዝሙት ከተባሉት የጨለማ ሥራዎች ሊያድነን መሆኑን ገና አላወቁም፡፡ ይልቁንም ቃሉ፡- “የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ÷ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምናይላል (ዘፀ. !.7)፡፡ የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ መጥራት ማለት በስሙ በተሰየሙ ቀናት ኃጢአትን መሥራት ነው፡፡ ይህ እግዚአብሔርን የኃጢአታችን ተባባሪ ማድረግ ነው፡፡ ፍርዱም ከፍ ያለ ነው።ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር ምህረቱ ሊነገር አይታሰብም ከቶም አይጀመርም። የዘመናት ጌታ ዘመኑ በተፈጸመ ጊዜ ከድንግል ተወልዶዓመተ ምህረትሰጥቶናልና። እንደ ዓባይ እንደ ጣና ባለ ባሕር ጽውዕ ምሉ ማር ጽውዕ ምሉ ቅቤ ቢጨምሩ ከመልኩ ከጣዕሙ እንደማይለውጠው ኹሉ የእኛም ኃጢአት የእግዚአብሔርን ቸርነት አይለውጠውም።
አንድም ወኃበ በዝንቱ ኃጢአት ህየ ፈድፈደት ጸጋሁ ለእግዚአብሔር እንዲል ኃጢአት ከበዛች ዘንድ የእግዚአብሔር ጸጋ በዛች። ሮሜ [1.!3] እንዴት ቢሉ በኃጢአቱ ቦታ ጽድቁ ስለገባ። አንድም ጌታ ሰው መኾኑ በምልአተ ኃጢአት ነው እንጂ በጥንተ አብሶ አይደለምና።/ከአዳምና ከሔዋን ዠምሮ በዘር የሚተላለፍ ኃጢአት ጥንተ አብሶ ይባላል/ በጥንተ አብሶ ሰው ኾኖ ቢኾን አዳምንና ሔዋንን ብቻ ለማዳን ሰው ኾነ እንጂ እኛስ በመስዋዕታችን በግዝረታችን በጸሎታችን ዳንን ባልን ነበር። ግዝረቱ መስዋዕቱ እንዳላዳነ ካሳየን በኋላ ከድንግል ተወልዶ ሰው ኾነ።
ኃጢአት ከበዛች ዘንድ የእግዚአብሔር ጸጋ በዛች! እንዲኽ ከኾነ የእግዚአብሔር ጸጋ ይበዛልን ዘንድ ኃጢአት እንስራ እንላለንን?  አንልም። ቸርነቱን አድንቀን በንስሐ እንመለሳለን እንጂ።

የጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ መወለዱ የዓለምን ታሪክ ለሁለት የከፈለ ነው፡፡ ዛሬ በክርስቶስ የሚያምነውም ሆነ የማያምነው ዓለም ዘመንን ሲቆጥር ከክርስቶስ ልደት በፊት ከክርስቶስ ልደት በኋላ እያለ ይቆጥራል፡፡ ለምን? ስንል ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ዘመን ለሁለት ስለከፈለው ነው፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረው ዘመን ዓመተ ፍዳ፣ ዓመተ ኵነኔ ሲባል ከክርስቶስ ልደት በኋላ ያለው ዘመን ግን ዓመተ ምሕረት ተብሏል፡፡

ዲያቢሎስ
በሥጋ ከይሲ ተሠውሮ ቢያስት ጌታችንም በሥጋ ብእሲ ሥግው ኾኖ አዳነን! አምስት ሺህ አምስት መቶ ዓመት ሲፈጸም ከእመቤታችን ያላባት መወለዱ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለናት መወለዱን ያስረዳል። ልደት ቀዳማዊ ተዓውቀ በደኃራዊ ልደት እንዲል። ሰብአ ሰገል በኮከብ እየተመሩ ወደ ቤተልሔም መጡ። ኮከብ የተባለው የማታ ኮከብ ሳይኾን መልአክ ነው። እንዴት ታወቀ ቢሉ እነኾ ኮከብ በማታ እንጂ በቀን አይታይም። ሰብአ ሰገልን ግን በቀን መራቸው። ኮከብ ወደ ምዕራብ ይሄዳል እንጂ ወደ ምስራቅ አይመራም። ሰብአ ሰገልን ግን ወደ ምስራቅ መራቸው። ኮከብ ርቀት አለው ሰብአ ሰገልን ግን ከአናታቸው ጥቂት ከፍ ብሎ መራቸው። ይህስ ኾኖ ለምን መልአኩ በኮከብ ተመሰላቸው ቢሉ ሰብአ ሰገል የኮከብ አጥኚ ወይንም አስትሮኖመርስ ስለነበሩ በለመዱት ነገር ለመሳብ ነው።
አውራ ጣቱን አሰረችው
እመቤታችን ጌታን በወለደችው ጊዜ የጌታን አውራ ጣት አስራ ነበር። ምሥጢሩ ምን ይሆን ቢሉ እነሆ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ እንዲህ አድርገው ይገንዙሃል ስትል ነው። አንድም መንፈስ እንዳይደለ ለማሳየት ነው። መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና አይታሰርም ነበር። አንድም በጨርቅ ጠቀለለችው። ይህም ምሥጢሩ አንድ ነው። (የዮሴፍና ኒቆዲሞስ መግነዝ መንፈስ አለመሆኑን ለማሳየት)

ወደ
ምሥራቅ ተመልከቱ፦
ዲያቆኑ
በቅዳሴ ላይ ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ ይላል ሕዝቅኤል በትንቢቱ እንዲህ አንዳለ፦በምሥራቅ የተዘጋ ጀጅ አየሁ; ይህች በር ተዘግታ ትኖራለች እንጂ አትከፈትም፤ ሰውም አይገባባትም የእስራኤል ቅዱስ ሳይከፍት ገብቶ ሳይከፍት ወቶባታልናሕዝቅኤል #4.1
ምሥራቅ
እመቤታችን ናት መናፍቃኑ ግን ይህማ ስለቤተመቅደስ የተነገረ ነው ይላሉ; ተዘግቶ የሚኖር ቤተመቅደስ አለ እንዴ? ሰውም የማይገባበት ቤተመቅደስ የለም፤ ይህማ ስለእመቤታችን የተተነበየ ነው። ከምሥራቅ ፀሐይ እንደሚወጣ ከምስራቋ እመቤታችን ፀሐይ ጌታ ተወልዷልና። አንድም ይህች በር ተዘግታ ትኖራለች እንጂ አትከፈትም አለ; ድንግል በክልኤት ናትና; በሥጋም በነፍስም ድንግል ናትና ቅድመ ፀኒስ ወሊድ ድንግል ጊዜ ፀኒስ ወሊድ ድንግል ድህረ ፀኒስ ወሊድ ድንግል ናትና; ወትረ ጊዜ ድንግል ናትና ሲል ነው። አንድምሰውም አይገባባትምአለ አንድያ ልጇን ብቻ ወልዳለችና። የእመቤታችን ክብርማ መቼ ተነገረና? የእመቤታችን ፍቅርማ መቼ ተነግሮ ይፈጸምና? ስለፍቅሯ ለመዘመር ለመቃኘትሞከሩ ግን መቼ የእናቴ ፍቅር በቀላሉ ይነገርና? መቼ እንዲህ በቀላሉ?
ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት

እግዚአብሔር
ፅዮንን መርጧታልና፤ ዛቲ ይዕቲ ምዕራፍየ ለዓለም (ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት) መርጫታለሁና በእርሷም አድራለሁ። መዝ )"1.03
ሐዋርያው
ዮሐንስቃልም ሥጋ ሆነእንዳለ ጌታችን ከእመቤታችን ሥጋን ነስቶ ተወለደልን። ከእመቤታችን የነሳው ቅዱስ ሥጋ ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ ብሎ ዐረገ። ክርስቲያን ሆይ ከእመቤታችን የተነሳው ቅዱስ ሥጋ ወደሰማይ ዐርጓል እንጂ በምድር ተቀብሮ በስብሶ የቀረ እንዳይመስልህ። ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት እንዲል።
ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ አለ፦
በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ … “ቃልም ሥጋ ሆነ” [ዮሐ 1.1]
በመጀመሪያ ቃል ነበረ፦በመጀመሪያየሚለው ቃልበመጀመሪያእግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ ከሚለው ይለያል፤ [ዘፍ1.1] ሰማይና ምድር ለመፈጠር የተወሰነ ጊዜ ነበራቸው፤ በመጀመሪያ ቃል ነበረ የሚለው ግን በሰውኛ አገላለፅ እንዲገባን ነው እንጂ የተወሰነ ጊዜን አያመለክትም። ቁጥር እንኳን መጀመሪያና መጨረሻ የለውም፤ ቃል [ወልድ ዋህድ ኢየሱስ ክርስቶስም] የመጀመሪያው አልፋ የመጨረሻው ዖሜጋ ነው። ራዕ !2
በመጀመሪያ
ቃል ነበረ አዎ ያም ቃል እግዚአብሔር ነበረ! ሥጋንም ለበሰ፤ ከማን? ከማን ሥጋን ነሳ? ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በኤፍራታ በቤተልሔም ተወለደ!! ልበአምላክ ዳዊት ናሁ ሰማዕናሁ በኤፍራታ መዝ. [131:6] እነሆ በኤፍራታ ሰማነው እንዳለ ከሀገር ለይቶ በቤተልሔም ከቦታ ለይቶ በከብቶች ግርግም ከሴቶች ለይቶ ከእመቤታችን ተወለደ። ህጻን ተወልዶልናል ወንድ ልጅም ተሰቶናል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘላለም አባት የሠላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ኢሳይያስ 9.6
እንኳን
ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን!

***//***

የጌታችን
ልደት መልእክት!

አንዱ
ሸረፌ የሚባል ባለጸጋ ነበር። ሹሙን ጠርቶ በቀን በቀን ፩ድ ወቄት ዱቄት ለድኾች ሳትሰጥ አትዋል አለው። ቢሰጥ እየበዛ ሔደ። ከበዛስ ብሎ ከታዘዘው አብልጦ ወቄት ዱቄት ይሰጥ ዠመር። ባለጸጋው ከቤተ መዛግብቱ ቢገባ ንብብረቱ በዝቶ አገኘው። ሹሙንም ያዘዝኹህን ትተሃል እንዴ? ሲል ጠየቀው። ሹሙም እንዲያውም አብልጬ እሰጣለሁ አለው። እንግዲያው አትገምግም እጅህ እንዳነሳ ስጥ ብሎታል።
የተቸገረ ብታይ ከንፈር ከመምጠጥ የቻልካትን ትንሿን አድርግለት! ሐዋርያው በሥራና በምግባር እንጂ በቃል ብቻ አንዋደድ እንዲል ለድኾች የቻልነውን እንስጥ! በየበአላቱ ዶሮ በማይጮኽበት ጢስ በማይጤስበት ቤት ያለችንን ተካፍለን እንብላ! ትዝ ይለኛል ልጅ እያለኹ እንደ ልደተ ክርስቶስ ባሉ በዓላት ላይ ከክፍል ጓደኞቼ ጋር ዶሮ እያሰራን ለድኾች እናበላ ነበር።