ዜና


የገንዳ ውሀ ከተማ ወረዳ ቤተ ክህነት ሰበካ መንፈሳዊ ጠቅላላ ጉባኤ ጉባኤ ተካሄደ!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሰሜን ጐንደር ሀገረ ስብከት የገንዳ ውሀ ከተማ ወረዳ ቤተ ክህነት ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ተካሄደ፡፡ ህዳር 10/2005 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ጀምሮ የተካሄደው ስብሰባ በሁለት አጀንዳዎች ላይ በማተኮር ውይይቱን አካሂዷል፡፡ የመጀመሪያው አጀንዳ የ2004 በጀት አመት ስራ አፈፃፀም ግምገማ ሲሆን ሁለተኛው አጀንዳ ደግሞ የአስተዳደር ጉባኤ አባላት ምርጫ እንደነበር ተገልጧል፡፡
በስብሰባው ወቅት የ2005 በጀት አመት ስራ አፈፃፀም እቅድ እንዲዘጋጅ፣ የአብያተ ክርስቲያናት ህንፃ ግንባታ ስራዎች ትኩረት ተሠጥቶ ቅደም ተከተል እንዲበጅላቸው፣ በአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የተፈጠሩ አስተዳደራዊ ችግሮች እንዲፈቱ የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተጠቁሞበታል፡፡
ስብሰባው በጸሎት ተጀምሮ ቃለ እግዚአብሔር ከተሠማ በኋላ የተካሄደ ሲሆን በቤተ ክህነቱ የተፈጠሩ ችግሮች በቶሎ መቀረፍ እንዲችሉ የጉባኤ አባላት ተከታታይ ውይይት እንዲያደርጉና ውጤታማ ስራዎች እንዲሰሩ አስተያየት የተሠጠ ሲሆን ጉባኤው የተጠናቀቀው በጸሎት እንደነበር ተመልክቷል፡፡

No comments:

Post a Comment