Pages

Monday, November 5, 2012

''በስመ ሥላሴ ''
''ጉዞ ወደ ምድረ ግብፅ''
+++++ከዚህ በኋላ ራፋን ወደተባለ አገር ሄዱ ::የራፋን ሰዎች መለከት እየነፉ ወጥተው እመቤታችንን ዮሴፍን እና ሰሎሜን በድንጋይ ቀጠቀጧቸው ::እነ ዮሴፍ ከዚያ አገር ወጥተው ሄዱ ::በአረብ አንፃር ቄድሮስ ከተባለ አገር ደረሱ ::በተቃራኒው የሚጾሙ የሚጸልዩ ደጋግ ሰዎችን አገኙ አገሩም በጣም ደስ የሚያሰኝ ልምላሜ የተሞላበት ነበር በቄሮስ 8 ወር ተቀመጡ ::ዮሴፍም እመቤታችንን ሁሉን ነገር ትተን ከዚህ አገር እንቀመጥ አላት አገር ለአገር ዋሻ ለዋሻ መንከራተቱን ትተን እንረፍ ማለቱ ነው ::እመቤታችንም ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ እዚህ መቀመጥ አንችልም አለችው ::
በዚያች ሌሊት ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ እመቤታችንን ከዚህ አገር ውጪ አላት ከዚያም አገር ወጥተው ወደ ደብረ አሞር ሄዱ ::የተለያየ ደዌ የያዛቸው ሰዎች ወጥተው ተቀበሏቸው እመቤታችን ሁሉንም ፈወሰቻቸው እነዮሴፍ በደብረ አሞር ብዙ ጊዜ ተቀመጡ ::
ከደብረ አሞር ወጥተው ሲሄዱ ጌላውዳ ከተባለ አገር ደረሱ በዚያም ርኩስ መንፈስ ያደረበት ሰው አገኙ ::ርኩስ መንፈስ ከያዘው 70 ዓመት አልፎታል ::ሰውየው አይተኛም ሥጋውን በድንጋይ ይቦጫጭቃል በሰንሰለትም ሲታሰር ሰንሰለቱን ይሰባብራል ::እመቤታችንን ባያት ጊዜ ይቅር በይኝ ብሎ ከእግሯ ስር ወደቀ ::
እመቤታችንም ርኩሱን መንፈስ በእግዚአብሔር ስም ውጣ አለችው ::ርኩሱም መንፈስ ወጣ ርኩሱ መንፈስ ጦጣ ይመስል ነበር ክፉ አራዊት የርኩሳን መናፍስት መገለጫዎች ናቸው ::ዮሐንስም በእባብና በዘንዶ ዲያብሎስን ሲገልጽ እንዲህ ይላል ::''ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ ''የዮሐንስ ራዕይ 12:9 ርኩሱ መንፈስ የወጣለት ሰው ከአንቺ አልለይም ብሎ እየሰገደ እመቤታችንን ተከተላት ::እመቤታችንም ወደ ዘመዶችህ ተመልሰህ እግዚአብሔር ያደረገልህን ንገር አለችው ::
እመቤታችን የተለያዩ ተአምራትን እንደምታደርግ በአካባቢው ተሰማ :: አንድ ሆዱን የነፋው ሀገረ ገዢ መጥቶ ፈውሺኝ አላት ::እመቤታችንም በልጄ እመን ትድናለህ አለችው እርሱም አምናለሁ አለ ከሆዱም እባብ ወጣለት ከበሽታውም ተፈወሰ ::እነ ዮሴፍን ዘጠኝ ወር ያህል ከቤቱ አስቀመጣቸው ::ከዘጠኝ ወር በኋላ ከቤቱ ወጥተው ሲሄዱ ሊባ የሚባል ባሕር ካለበት አገር ደረሱ የዚያ አገር ሰዎች በጅራፍ እየገረፉ አባረሯቸው ::እነዮሴፍ ቤልቤል ከሚባል ዛፍ ስር አደሩ ::ነገር ግን መልአክ ወርዶ በሰረገላ ወስዶ ካሳደድዋቸው ሰዎች አገር መካከል አስቀመጣቸው ::
እመቤታችንም ከእንቅልፏ በነቃች ጊዜ ያደሩበት አገር በጅራፍ እየተገረፉ ያሳደዷቸው ሰዎች አገር እንደሆነ አወቀች ::እመቤታችንም የትናንቱ ጅራፍ ተመልሶ እንዳይመጣ ወደ እግዚአብሔር አጥብቃ ጸለየች በጅራፍ የገረፏቸው ሰዎችም ከሰውነት ወደ ውሻነት ተለውጠው ውሻ ሆኑ :: እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ሰዎች የሚቀጣበት መሣሪያው የተለያየ ነው አእምሮ ያለውን ሰው አእምሮ የሌለው እንሰሳ ያደርገዋል ::ይህ አይነት ቅጣት በጣም የሚታበዩ ሰዎች የሚቀጡበት ነው :: የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በትዕቢቱ ምክንያት ወደ አውሬነት ተለውጦ ቤተ መንግሥቱ ለቅቆ ከአራዊት ጋር ሣር እየበላ ሰባት ዓመት ኖርዋል :: ትንቢተ ዳንኤል 4:28-34
''የእመቤታችን ለቅሶ በወንዝ ማዶ ''=>ይቆየን
ወስብሃት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
''ያስተማረን ልዑል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ''አሜን !!!

No comments:

Post a Comment