በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን፡፡
‹‹እንኳን ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል አመታዊ
ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ!!››
እንሆ ህዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም እንደ ወትሮው
ሁሉ የቅዱስ ሚካኤል በዓል በመላው አለም በሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ዘንድ በድምቀት ይከበራል፡፡ በሰሜን ጐንደር ሀገረ
ስብከት ገንዳውሀ ከተማ ወረዳ ቤተ ክህነት አከባቢ የምንገኝ መእመናንም በዓሉን ከዋዜማው ጀምሮ በታላቁ የገንዳ ውሀ ቅዱስ ሚካኤል
ቤተ ክርስቲያን ተገኝተን እናከብረዋለን፡፡
ስለሆነም ቤተ ክርስቲያን የመንፈሳዊውን አገልግሎት
ድግስ አሰናድታ ሁላችንም የአካባቢው ምእመናን እንድንታደምበት ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡
ኑ ከቅዱስ ሚካኤል ረድኤት በረከት ተሳተፉ!!
በ11/03/2005 ዓ.ም
ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ
ዋዜማ፤
ምሽት 12፡00-3፡00 የወጣቶች/ሰ/ት/ቤት ጉባኤ፤
ከ3፡00 ሠዓት - ንጋቱ 12፡00 ሠዓት ማህሌት፤
በእለቱ
ከ12፡00 – 6፡00 ሠዓት ስብከተ ወንጌልና
ኡደት /ንግስ/፤
ከቀኑ 6፡00 – 9፡30 ሠዓት ስርዓተ ቅዳሴ ይከናዎናል፡፡
በቅዱስ ሚካኤል ረድኤት እግዚአብሔር ሐገራችን ኢትዮጵያን ይባርክ!!!
ቤተ ክርስቲያናችን ይባርክ!!!
No comments:
Post a Comment